አዲሰ አበባ/ፊንፊኔ እና Cosmopolitan (Global citizen)


በቶማስ ሰብሰቤ

አዲስ አበባ መሬት ፣ ህዝብና የመንግስት አስተዳደር ያካተተች የኢትዮጵያ ከተማ ናት። ስለ አዲስ አበባ የትኛውንም መብት ስናነሳ ሶስቱንም ያካተተ መሆን አለበት።መሬቱን ወዶ ህዝቡን ማራቅ አይቻልም ፤ ህዝቡን እያራቁ መሬቱን ይገባኛል ማለት አይቻልም።ለእኔ አዲስ አበባዊነት ብሄር አልባ ነው።ከተማይቱ የመላው የሀገሪቱን ገፅታ የምታሳይ ናት።አዲስ አበቤዎች cosmopolitan or Global citizen ናቸው።ከተማዋ የብሄር፣ የሃይማኖት ፣ የማንነት ጋር የተያያዘ ፖለቲካ የላትም።ስለ ነዋሪው ካወራን ከዚህ የዘለለ ሀቅ የለም።

Fig-1-Map-of-Addis-Ababa-City

“A cosmopolitan community might be based on an inclusive morality, a shared economic relationship, or a political structure that encompasses different nations.ከኦሮሚያ ፣ከአማራ ፣ትግሬ ፣ደቡብ ፣ጋንቤላ ፣ሱማሌ ፣አፋርና ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጣ ትውልድ ያለባት cosmopolitan community ወይም ቅይጥ ህዝብ ያለባት አዲስ አበባ /ፊንፊኔ/ጲንጲኔን የምናየው ሀቅ ነው። በ cosmopolitan community የሚመደብ ከተማ አይነተኛ መሰፈርቱ በዛች ከተማ ያለው ነዋሪ 1.የተለያዮ ህዝቦች ከአንድ ሀገር መሰባሰብና 2. የራሱ የሆነ አንድ ወጥ ብሄር አልባ መሆን ነው።

“a cosmopolitan community individuals from different places”።ታዲያ አዲስ አበባ አንድ ወጥ የሆነ ብሄር ሳይኖራር ፤ ነዋሪውም ከአራቱም የኢትዮጵያ ክፍል ተሰባስቦ ለመሬት ሲባል ብቻ 6 ሚሊየን ህዝብ በግድ በብሄር ፖለቲካ ለማመስ መሞከር የሚያሳፍርና የማይቻልም ነው።ነፍጠኛ የአዲስ አበባ መሬት ወሮ ኢምፔሪያሊዝም አስፋፋ ካልን ወደ ከኋላ ተስበን ዛሬስ 6 ሚሊየን ህዝብን ለመጨፍለቅ ማስብ ኢምፔሊያሊዝም በሌላ መልክ አይደል እንዴ!✋✋

Fig-1-Map-of-Addis-Ababa-City

የአዲስ አበባ ህዝብ አለማቀፋዊ ድባብ አለው።ማንነቱ የብሄር አይደለም።ማንነቱ በምንም ሳይለካ የተለያዪ ህዝቦች የሚኖሩበት ነው።ዛሬ ከኢህአዴግም የወጣው አዋጅ ህዝቡን የማይመስል ነው።ህዝቡ ብሄር የለውም።ህዝቡ ከማንም ጋር በብሄር አይመሳሰልም ፣በራሱ ራሱ እየተግባባ የሚኖር ነው።

የአዲስ አበባ ህዝብ ረስቶ ስለ አዲስ አበባ ማውራት አይቻልም።ስለ መሬት ብሎ ህዝብ ማራቅ ከባድ ነው።ህዝብ ከማንም ይበልጣል።6 ሚሊየን ህዝብ በኢህአዴግ ተረግጣል።ኢህአዴግ ለኦሮሞ ህዝብ አስቦ ሳይሆን ለራሱ ብሎ ቅይጡን ህዝብ ድምፅ አይስማም።ታዲታ መዚህ መልኩ መፍትየው ማን ጋር ነው።የአዲስ አበባ መፍትሄ በአዲስ አበባ ነው።

images

የአዲስ አበባ ህዝብን ንቆ መሬቱን መውደድ አይቻልም።ትላንት አባቱ ያንን አድርገ ብሎ ዛሬ መጨፈር አይቻልም።የድሮ ድሮ ነው።ዛሬ ዛሬ ነው።አባት በሰራው ልጅን መቅጣት አይቻልም: አይገባም።ስለዚህ መፍትሄው አዲስ አበባ ከብሄር ውጪ ማስቀጠልና አለም አቀፋውነታን ማስጠበቅ ነው።ሸገር ብሄር ሳይኖራት በግድ ለማድረግ መሞከት ግን አላዋቂነት ስለሆን የማይሳካ ነገር መሞከር ተገቢ አይደለም።ለመግባባት መነጋገር ወሳኝ ነቅ።

ኢህአዴግ አዲስ አበባ ላይ ያወጣው አዋጅ ነገ ላይ መዘዝ የሚያመጣ ነው እንጂ መፍትሄ የለውም።ነገ ህዝባው እልቂት ለመፍጠር ዛሬ ላይ የተሰራ እርሾ ነው።አዱ ገነት የኦሮሞ መሬት ቢሆን እንካን ህዝቡ ግን ቅይጥ ነው።ህዝቡን አንድ አፋ እንዲናገት መሞከር ግን የማይቻል ነው።ኦሮምኛ ማስተማርና አማርኛ ማጥፋት መፍትሄ አይሆንም።መንጋገር ካለ መግባባት ይመጣል።

 

This entry was posted in ጉዳዮች - Affairs, Tomas Sebsibe. Bookmark the permalink.

Any comment - አስተያየት ካለዎ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s