ለእኔ ዱለት ፤ ለእሱ ክትፎ!


በቶማስ ሰብሰቤ (ጋዜጠኛ)

ግብርን በጣም በተጠና ሳይንሳዊና የቋንቋ ፍቺ መሰጠት ሳይሆን በአጭር ነገር መግለፅ አማረኝ።በቃ አጭር ቃል።ግብር ምን ይገልፀዋል?  ገባሪና አሰገባሪን ምን ያመሳስለዋል?  ምን ይለያየዋል? የገባሪና የአስገባሪ ኑሮስ እንዴት ፍትው ብሎ ይታያል? ግብር ምን ያህል ሰውን እየገጎዳ ለመንግስት እየጠቀመ ነው? ግብር ለምን ይጠላል? የሚገበረው ለእኛ ከሆነ ለምን ወደ ሃላ አስባለን ወዳጄ?

Tax-Time-Photo-630x363

ግብር በአጭር ገላፅ ሀሳብ ማሰቀመጥ ፍለጋ ላይ ነኝ።የምጠቀመው ቃል የገባሪውነወ ሮሮ የሚያሳይ ፤ የአስገባሪውን ጥቅም የሚያሳይ ቢሆን ደስ ይለኛል? ወዳጄ! ግብር ቀላል አይምሰልሽ የአለማችን የሺ ዘመን ታሪክ ግብር ነው።ትገብራለህ አትገብርም ነው? ከሮም ፣ግብፅ ፣አክሱም ፣ባቢሎን ስልጣኔ ድረስ የተማርነው ታሪክ የግብር ጦርነት ነው! በዚህ ዘመንም በካፒታሊዝምና ሶሻሊዝም ጎራ የግብር ፍቅር አለ ወዳጄ!

ወዳጄ ገባሪ ግብት ሲበዛበት ግን አያሰቀምትህም።በድሮ ዘምን ጪሰኛው ያምፃል ።ገባሪ ሲቆጣ ንጉስን ያባራል።ገባሪ ላይ ፍትሃዉ ያልሂነ ፣አቅሙን ያላማከለ ፣እሱን የማይመሰለው ግብር መጣል ያበዛ መንግስት መጨረሻው ልክ እንደ አንበሳው ይሮጣል።ንግስናው በራሱ እጅ በህዝብ ያጣል።

889009FB_IMG_1495994705192

ግብር አንባገነኑም ፣ዲሞክራቱም የሚፈደባደብለት ነው።እና ይህ የሺ ዘመን የመንግስት ውለታ፣  የሺ ዘምን የነዋሪ “መጣ እንዴ” የሚባለው ግብር በአንዲት ቃል መግለፅ ይከብዳል።ባይሆን ግብር መሳየት በአጭር ነገር መልካመ ነው።ግብር ግዴታ ፣ አሰፈላጊ፣ ጤና ፣መንገድ ፣ ትምህርት ቤት ፣ዝርፊያ ፣ህዝብን ማናገላቻ ልለቅ ፈለኩና ሙሉ አይደሉም ብዮ ዝም።ብቻ ግብር የሆነ አይነተኛ ጥቅም ያለው ግን ሚዛናዊነት ካጣ የሚጠላ እፋ ሰለሆነ ፍለጋዮን ቀጠልኩ።በመጨረሻም ትዝ ያለኝ ይህ ነው ግብር ማለት ለራስህ ጉለት ፤ ለመንግስት ክትፎ መጋበዝ ማለት ነው።👏👏👏👏

This entry was posted in ጉዳዮች - Affairs, Tomas Sebsibe. Bookmark the permalink.

Any comment - አስተያየት ካለዎ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s