አዲሰ አበባ/ፊንፊኔ እና Cosmopolitan (Global citizen)


በቶማስ ሰብሰቤ

አዲስ አበባ መሬት ፣ ህዝብና የመንግስት አስተዳደር ያካተተች የኢትዮጵያ ከተማ ናት። ስለ አዲስ አበባ የትኛውንም መብት ስናነሳ ሶስቱንም ያካተተ መሆን አለበት።መሬቱን ወዶ ህዝቡን ማራቅ አይቻልም ፤ ህዝቡን እያራቁ መሬቱን ይገባኛል ማለት አይቻልም።ለእኔ አዲስ አበባዊነት ብሄር አልባ ነው።ከተማይቱ የመላው የሀገሪቱን ገፅታ የምታሳይ ናት።አዲስ አበቤዎች cosmopolitan or Global citizen ናቸው።ከተማዋ የብሄር፣ የሃይማኖት ፣ የማንነት ጋር የተያያዘ ፖለቲካ የላትም።ስለ ነዋሪው ካወራን ከዚህ የዘለለ ሀቅ የለም።

Fig-1-Map-of-Addis-Ababa-City

“A cosmopolitan community might be based on an inclusive morality, a shared economic relationship, or a political structure that encompasses different nations.ከኦሮሚያ ፣ከአማራ ፣ትግሬ ፣ደቡብ ፣ጋንቤላ ፣ሱማሌ ፣አፋርና ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጣ ትውልድ ያለባት cosmopolitan community ወይም ቅይጥ ህዝብ ያለባት አዲስ አበባ /ፊንፊኔ/ጲንጲኔን የምናየው ሀቅ ነው። በ cosmopolitan community የሚመደብ ከተማ አይነተኛ መሰፈርቱ በዛች ከተማ ያለው ነዋሪ 1.የተለያዮ ህዝቦች ከአንድ ሀገር መሰባሰብና 2. የራሱ የሆነ አንድ ወጥ ብሄር አልባ መሆን ነው።

“a cosmopolitan community individuals from different places”።ታዲያ አዲስ አበባ አንድ ወጥ የሆነ ብሄር ሳይኖራር ፤ ነዋሪውም ከአራቱም የኢትዮጵያ ክፍል ተሰባስቦ ለመሬት ሲባል ብቻ 6 ሚሊየን ህዝብ በግድ በብሄር ፖለቲካ ለማመስ መሞከር የሚያሳፍርና የማይቻልም ነው።ነፍጠኛ የአዲስ አበባ መሬት ወሮ ኢምፔሪያሊዝም አስፋፋ ካልን ወደ ከኋላ ተስበን ዛሬስ 6 ሚሊየን ህዝብን ለመጨፍለቅ ማስብ ኢምፔሊያሊዝም በሌላ መልክ አይደል እንዴ!✋✋

Fig-1-Map-of-Addis-Ababa-City

የአዲስ አበባ ህዝብ አለማቀፋዊ ድባብ አለው።ማንነቱ የብሄር አይደለም።ማንነቱ በምንም ሳይለካ የተለያዪ ህዝቦች የሚኖሩበት ነው።ዛሬ ከኢህአዴግም የወጣው አዋጅ ህዝቡን የማይመስል ነው።ህዝቡ ብሄር የለውም።ህዝቡ ከማንም ጋር በብሄር አይመሳሰልም ፣በራሱ ራሱ እየተግባባ የሚኖር ነው።

የአዲስ አበባ ህዝብ ረስቶ ስለ አዲስ አበባ ማውራት አይቻልም።ስለ መሬት ብሎ ህዝብ ማራቅ ከባድ ነው።ህዝብ ከማንም ይበልጣል።6 ሚሊየን ህዝብ በኢህአዴግ ተረግጣል።ኢህአዴግ ለኦሮሞ ህዝብ አስቦ ሳይሆን ለራሱ ብሎ ቅይጡን ህዝብ ድምፅ አይስማም።ታዲታ መዚህ መልኩ መፍትየው ማን ጋር ነው።የአዲስ አበባ መፍትሄ በአዲስ አበባ ነው።

images

የአዲስ አበባ ህዝብን ንቆ መሬቱን መውደድ አይቻልም።ትላንት አባቱ ያንን አድርገ ብሎ ዛሬ መጨፈር አይቻልም።የድሮ ድሮ ነው።ዛሬ ዛሬ ነው።አባት በሰራው ልጅን መቅጣት አይቻልም: አይገባም።ስለዚህ መፍትሄው አዲስ አበባ ከብሄር ውጪ ማስቀጠልና አለም አቀፋውነታን ማስጠበቅ ነው።ሸገር ብሄር ሳይኖራት በግድ ለማድረግ መሞከት ግን አላዋቂነት ስለሆን የማይሳካ ነገር መሞከር ተገቢ አይደለም።ለመግባባት መነጋገር ወሳኝ ነቅ።

ኢህአዴግ አዲስ አበባ ላይ ያወጣው አዋጅ ነገ ላይ መዘዝ የሚያመጣ ነው እንጂ መፍትሄ የለውም።ነገ ህዝባው እልቂት ለመፍጠር ዛሬ ላይ የተሰራ እርሾ ነው።አዱ ገነት የኦሮሞ መሬት ቢሆን እንካን ህዝቡ ግን ቅይጥ ነው።ህዝቡን አንድ አፋ እንዲናገት መሞከር ግን የማይቻል ነው።ኦሮምኛ ማስተማርና አማርኛ ማጥፋት መፍትሄ አይሆንም።መንጋገር ካለ መግባባት ይመጣል።

 

Posted in ጉዳዮች - Affairs, Tomas Sebsibe | አስተያየት ያስቀምጡ

ድምፅ አልባዋ አዲስ አበባ!


በቶማስ ሰብስቤ

Fig-1-Map-of-Addis-Ababa-City

በሰሞነኛው «የኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላት ልዮ ጥቅም» አዲስ አበባ ያገለለ ነው።የአዲስ አበቤ ነዋሪዎች ያልተደመጡበት ነው።ለዚህ የሚጠቀሱ ብዙ ምክንያቶች አሉ።አንደኛው የከተማይቱ ምክር ቤት አባላት 99 በመቶ የክልል ሰዎች ሆነው በከተማይቱ ያደጉ ፣የተማሪና ስራ የተቀተሩ ናቸው።በዚህም ያገባኛል የሚል ሰሜት ያለው ነዋሪው ጋር ብቻ ነው።ተመራጭ ስለ ከተማዋ ህዝብ እንዲሰማው መጀመሪያ የከተማውን ህዝብ ሁለንተናው ሊረዳ ይገባል።ከተማዋን ሳይረዳ እንዴት ለአዲስ አበባ ይጨነቃል?  የአዲሰረ አበባ ህዝብ አስተሳደብና የህይወት ውሎ ሌላ የመሪው ሚና ሌላ ታዲያ እንዴት ይጣጣማል?

በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ህዝብ ትልቁ ነው።ህዝብ ትልቁ ነው ሲባል ተደማጭ ነው ማለት ነው።ታዲያ ህዝብ የሚደመጥ ከሆነ የታል አዲስ አበቤዋች የተደመጡት?  ዲሞክራሲ አለ ካልን ሸገሮች የመረጣቸው ሹሞች ለምን ከህዝቡ በተቃራኒ ቆሙ? ለዚህ መልሱ አንድ አንድ ነው።የእኛ ዲሞክራሲ ከህዝብ ጋር ሳይሆን ከመሪው ፓርቲ ፍላጎት ጋር የሚሄድ ነው።ህዝቡ ሳይጠየቅ ስለ አዲስ አበባ መወያየት ምን የሚሉት ነው?

images

አዲስ አበባ የሚባለው እኮ መሬቱ ብቻ ሳይሆን ነዋሪውም ነው።ታዲያ መሬቱ የኦሮሞ ከሆነ ፤ ነዋሪውስ? በመሬቱ ብንስማማ በነዋሪውስ? ነዋሪው ጥያቄ መመለስ አለበት።አዲሰረ አበባ የአዲስ አበቤዎች ነው።ኦሮሞ በአዲስ አበባ ያለው ጥቅም ብቻ ሳይሆን ባለቤትነትም ይከበር ግን ኦሮሞን ለማስደሰት ነዋሪውን መርገጥ ተገቢ አይደለም።አዲስ አበባ የገነቡት መረገጥ የለባቸውም።ዛሬም ነገም ፍትህን የሚፈልግ ህዝብ ነው የአዲስ አበባ ህዝብ።

ሌላው ልዮ ጥቅም በህዝቦች መካከል ልዮነት ሲፈጥር እኩልነትንን ይንዳል።ህዝቦች በየትኛው ከተማ ሲኖሩ የእኔነት ሰሜት ሊኖራቸው ይገባል።ሀገር ማለት የራስ ነው።ሁሉም የሚደስትበት።አንደኛው ባዳነት የሚሰማው ከተማ መገንባት የለብንም።

ኢህአዴግ አንድነት አይወድም።ህዝብን ያራርቃል።የህዝብ መራራቅ ደሞበ የእሱ ስልጣን ያራዝምለታል።ይህ ደሞ የቆየ ያረጀ ስርዓት መጨረሻ ነው።በኦሮሞና አማራ ህዝብ መነገድ ስልቱ አድርጎታል።ዛሬ ደሞ ኦሮሞን የጠቀመ መስሎት አዲስ አበባ ላይ ሸፍጥ ሰራ።

ኢትዮጵያዊነት ይለመልናል።ህዝቦች ይቀጥላሉ።ስርዓት ይሞታል ፤ ታሪክ ግን ሁሉን ያስቀምጣል።የኢህአዴግ መቀበሪያ ሲደርስ እጨለመመበት ነው።

Posted in ጉዳዮች - Affairs, Tomas Sebsibe | አስተያየት ያስቀምጡ

የፌስ ቡክ አርበኛ ነን!!


የፌስ ቡክ አርበኛ ነን!!
This is division of Labor bro.

በቶማስ ሰብስቤ

facebook-600x600

በየትኛውም ለውጥ ውስጥ የሰራ ክፍፍል አለ። ፍትህ ፣ እኩልነት ፣አንድነት ፣ሰበዓዊ መብትና ዲሞክራሲ የተከበረባት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ሀገር ሁሉ ወታደር መሆን አለብት የምትል አይመስለኝም።በአድዋ ጦርነት ከንጉሱ እስከ የወታደሩ ምግብ አብሳይ ድረስ ፤ ከንጉሱ እስከ አራቱም አቅጣጫ ያለ ኢትዮጵያዊ ሁላ አርበኛ ነበሩ።ካህኑ በፀሎት አርበኛ ፣ እናት ልጆን ለሀገር የምትሰጥ አርበኛ ፣ነጋዴ ብሩን የሚሰጥ አርበኛ ፣ ባለቀለሜው በሀገር ፍቅር በታሰሩ ፊደላት የህዝቡን ወኔ የሚቀስቅስ አርበኛ ነበር።በአድዋ ጦርነት የስራ ክፍፍል ነበር።

የንጉስ ሚኒልክና የወታደሩ የሰራ ክፍፍል ይለያያል ፤ የህዝቡና የወታደሩም የስራ ክፍፍል እንደዛው።ነገር ግን በስራ ክፍፍል አይደለም ድላችንን ያጣጣምነው ።ጀግናም ሁን ምርኮ አንተ የጥቁር ህዝቦች ነፅብራቅ የሆነው የአድዋ አሸናፊ ነህ።የጅብዱ መጠን በእያንዳንዱ ቢለያይም ድሉ የሁሉም ነው ፤ ደስታው የጋራ ነው 【እኛም እኮ በአድዋ የላይ ጎራዴ ሳናነሳ በአባቶቻችን እንኮራ አይደል እንዴ】……እረ ገና እንኮራለን ሲያንሰን ነው!

ዛሬስ ምን አዲስ ነገር አለው።
The division of labor

በዛሬዋ ኢትዮጵያ ፍትህ ለማምጣት የተለያዮ የስራ ክፍፍል አለ።አንዱ ወታደር ፣አንዱ አማፂ ፣ሌላው በገንዘቡ ሲደግፍ ፣ ሌላው በእውቀቱ ሌላውን ሲቀይር ፣ የሰበዓዊ መብት ተሟጋችና ተቃዋሚ ፓርቲ በመመስረት ሊንቀሳቀስ ይችላል።አንዱ ጠብመንጃ ፤ አንዱ ብዕር ሊመዝ ይችላል።ሁለቱም አላማቸው አንድ ነው።ፍትህን ለማረጋገጥ ጠመንጃም የያዘው ፤ ብዕርም የያዘው አላማ ነው።ጠመንጃ የያዘውን ለሰው ፍትህ በብዕር ብቻ ነው የሚመጣው ማለት አትችልም ፣ብዕር ለያዘውም ፍትህ በጠብመንጃ ብቻ ነው ልትለው አትችልም።

ፍትህን ለማምጣት ጠመንጃም አንዱ ክፍል ነው ልትል ትችላለህ ፤ ብዕርም ሌላው ነው።የስራ ክፍፍል የሌለው ትግል አሸናፊ መሆን አይችልም።ሁልም በችሎታው ፣በተሰጦው ፣ በሚታምንበት መንገድ መታገል ካልቻለ የመጨረሻ አላማህን በጋራ ማሳካት ይከብደዋል።Adam Smith እንዳለው “Division of labor helps in bringing about the right man in the right place. When there are too many jobs, every man tries to get himself absorbed in a work, where he thinks himself to be best fitted. Thus, the chances of putting, square pegs in round holes are minimized.

ልክ ጠብመንጃ እንዳነሳው ወታደር እኔም ብዕሬን አነሳለው!!
Adam smith’s wealth of nation.

በጠመንጃ ትግል ውስጥ ከተራ የአካል ብቃት እስከ ህይወት መሰዋትነት እንደሚያስከፍል ሁሉ ብዕርህ ስታነሳም እንዳትፅፍና እዳትናገር የሚፈልግ መንግስትና አለ።ማንም የፌስቡክ አርበኛ ሲልክ እሱ ሀሳቡን ለመግለፅ ያለበትን ፍርሃትና እኔ ምን አገባኝነት የሚያመጣበት የህልና ተጠቃቂነት ከንግግሩ ተረዳው። ደጋግሜ መፃፌ ፣ደጋህሜ ሃሳቤን መግለፄ ግን በኢትዮጵያ ለሚመጣው ለውጥ የነጥብ ድርሻ ይኖረዋል።የታገስ ከሚስቱ ይወልዳል በሚለው አዳም ስሚዝም 【Adam Smith】ይመሰክራል።” Division of labor increases dexterity and skill of the workers. When a person continuously works at one task for a longer time, he becomes expert of that task.”

Posted in ጉዳዮች - Affairs, Tomas Sebsibe | አስተያየት ያስቀምጡ